ከጠላቶችህ ጋራ ጦርነት ልትገጥም ወጥተህ አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶህ በማረክህ ጊዜ፣
ከምርኮኞቹ መካከል መልከ መልካም ሴት አይተህ ብትማርክህ፣ ሚስትህ ልታደርጋት ትችላለህ።
እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ አንድም ጠላት ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጥቷቸዋልና።