Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘዳግም 20:17

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኬጢያዊውን፣ አሞራዊውን፣ ከነዓናዊውን፣ ፌርዛዊውን፣ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት ፈጽመህ ደምስሳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ መንጎች እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።

የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣

የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያንን፣ የጌርጌሳውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ነው።”

የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣

“የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያከናውን ርጉም ይሁን፤ ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከላከል የተረገመ ይሁን!

አማሌቃውያን የሚኖሩት በኔጌብ፣ ኬጢያውያን ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በኰረብታማው አገር፣ ከነዓናውያን የሚኖሩት ደግሞ በባሕሩ አቅራቢያና በዮርዳኖስ ዳርቻ ነው።”

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ በአሕዛብ ከተሞች ውስጥ፣ እስትንፋስ ያለውን ነገር አታስተርፍ።

አለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በአምላክህ በእግዚአብሔርም ላይ ኀጢአት ትሠራለህ።

ከተማዪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ስለ ሆነ ፈጽማችሁ አጥፉ እኛ የላክናቸውን ሰላዮች ስለ ሸሸገች ጋለሞታዪቱ ረዓብ ብቻና ከርሷ ጋራ በቤቷ ውስጥ ያሉት ሁሉ ይትረፉ።

የምትሰበሰቡትም የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ እንዲሁም የሰዎችን ሁሉ፣ ይኸውም የጌቶችንና የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ እንድትበሉ ነው።”




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች