አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በማናቸውም ከተማ ፋሲካን መሠዋት አይገባህም፤
የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።
እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ፋሲካ አድርገህ ሠዋው።
በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማንኛውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቈይ አታድርግ።
ነገር ግን ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ፣ ፀሓይ ስትጠልቅ ምሽቱ ላይ ከግብጽ በወጣህበት ሰዓት፣ በዚያ ፋሲካን ሠዋ።