Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘዳግም 15:21

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፣ ዐንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማንኛውም ዐይነት ከባድ ጕድለት ያለበት ከሆነ፣ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ ‘መባው በሚቃጠል መሥዋዕትነት ከላሞች መንጋ መካከል የሚቀርብ ከሆነ፣ ነቀፋ የሌለበትን ተባዕቱን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያቅርበው።

እንከን የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።

እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች