በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ሁሉ ክንፍና ቅርፊት ያለውን መብላት ትችላላችሁ፤
ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው።
ዐሣማም እንደዚሁ ርኩስ ነው፤ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም፣ ስለማያመሰኳ፣ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ።