እግዚአብሔርም እናንተ ያላችሁትን በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ ማለም፤
እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።
ስለዚህ እንዲህ ብዬ በቍጣዬ ማልሁ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።”
ደግሞም ከምድር ሁሉ ይልቅ ውብ ወደሆነችው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ሰጠኋቸውም ምድር እንደማላስገባቸው እጆቼን አንሥቼ በምድረ በዳ በፊታቸው ማልሁ፤
“እናንተ የኀጢአተኞች ልጆች ይኸው በአባቶቻችሁ እግር ተተክታችሁ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ይበልጥ እንዲቈጣ ታደርጋላችሁ።
ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?