ንጉሡም ለኮከብ ቈጣሪዎቹ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕልሙንና ትርጕሙን ባትነግሩኝ አካላችሁ እንዲቈራረጥና ቤቶቻችሁም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆኑ ወስኛለሁ፤
የበኣልን ማምለኪያ ምስል ቀጠቀጡ፤ የበኣልንም ቤተ አምልኮ አፈረሱ፤ ይህንም ሕዝቡ እስከ ዛሬ ድረስ የኵስ መጣያው አድርጎታል።
ደግሞም ይህን ትእዛዝ የሚለውጥ ማንም ሰው ቢኖር፣ ከቤቱ ምሰሶ ተነቅሎ በምሰሶው ላይ እንዲሰቀል፣ ስለ ወንጀሉም ቤቱ የቈሻሻ መጣያ እንዲሆን አዝዣለሁ።
“እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤ አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።
ፈጥኖ እንደሚያልፍ ወራጅ ውሃ ይጥፉ፤ ቀስታቸውን ሲስቡ ፍላጻቸው ዱልዱም ይሁን።
ይህም ንጉሡን እጅግ አበሳጨው፤ አስቈጣውም፤ በባቢሎን ያሉ ጠቢባን ሁሉ እንዲገደሉም አዘዘ፤
ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገሩ ሕዝቦችም ሆኑ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ይቈራረጣሉ፤ ቤቶቻቸውም የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዣለሁ።”
እኔም እንዲህ አልሁት፤ “የጠቢባን አለቃ ብልጣሶር ሆይ፤ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ እንዳለ ዐውቃለሁ፤ ምንም ዐይነት ምስጢር አያስቸግርህም፤ ያየሁት ሕልም እነሆ፤ ተርጕምልኝ።
በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ።
በዚያ ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህች ከተማ ኢያሪኮን መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤ “መሠረቷን ሲጥል፣ የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣ የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።
ሳሙኤልም፣ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፣ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቈራረጠው።