የሰሜኑም ንጉሥ፣ የደቡቡን ንጉሥ ግዛት ይወርራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል።
ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጐርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባሉ።
“ከዚያም የደቡቡ ንጉሥ በቍጣ ወጥቶ የሰሜኑን ንጉሥ ይወጋል። የሰሜኑ ንጉሥ ታላቅ ሰራዊት ቢያሰባስብም ይሸነፋል።
“የደቡቡ ንጉሥ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፤ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል።
አማልክታቸውን፣ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ የከበሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካል፤ ወደ ግብጽም ይወስዳል። ለጥቂት ዓመታትም ከሰሜኑ ንጉሥ ጋራ ከመዋጋት ይቈጠባል።
የባለ ጥቍር ፈረሶች ወደ ሰሜን፤ የባለ ነጭ ፈረሶች ወደ ምዕራብ አገር፣ የባለዝጕርጕር ፈረሶች ወደ ደቡብ አገር ይወጣል።”
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”