በገዛ አገሩ ወዳሉት ምሽጎችም ፊቱን ይመልሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ይወድቃል፤ ዳግምም አይታይም።
እንደ ሕልም በርሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።
ያለ ምንም ጥያቄ ኀያላንን ያንኰታኵታል፤ ሌሎችንም በቦታቸው ይሾማል።
ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።
ክፉና ጨካኙን ሰው፣ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤
ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ ብፈልገውም አልተገኘም።
ምድር እንደ ሰካራም ዞረባት፤ ነፋስ እንደሚወዘውዘውም ጐጆ ሆነች፣ የዐመፅዋ ሸክም ከባድ ስለ ሆነ ትወድቃለች፤ እንደ ገናም አትነሣም።
“ፈጣኑ መሸሽ አይችልም፤ ብርቱውም አያመልጥም፤ በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ ተሰናክለው ወደቁ።
መጨረሻሽን አሳዛኝ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም፤ ትፈለጊያለሽ፤ ከቶም አትገኚም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”
“ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሣል፤ የሰሜንን ንጉሥ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋራ ተዋግቶ ድል ያደርጋል።