“በዚህ ነገር ምድር አትናወጥምን? በውስጧ የሚኖሩትስ ሁሉ አያለቅሱምን? የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይፈናጠራል፤ ተመልሶም ይወርዳል።”
ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የተራሮችም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ።
የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዷል፤ እጁን አንሥቶ መትቷቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።
“ይህ እንደ አባይ ወንዝ ሙላት የሚዘልለው፣ እንደ ደራሽ ወንዝ የሚፈስሰው ማነው?
ግብጽ እንደ አባይ ወንዝ ሙላት ይዘልላል፤ እንደ ደራሽ ወንዝ ይወረወራል፤ ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ፤ ከተሞችንና ነዋሪዎቻቸውን አጠፋለሁ’ ይላል።
ሰው በዚያ መኖር እስከማይችል ድረስ፣ የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደው ስለሚጸና፣ ምድር ትናወጣለች፤ በሥቃይም ትወራጫለች።
ከስድሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም፣ ከተማውንና ቤተ መቅደሱን ይደመስሳሉ። ፍጻሜውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።
በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣ በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ ሕዝቡም ያለቅስለታል፤ በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣ አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤ በምርኮ ከእነርሱ ተወስዷልና።
ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤ የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣ የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።
ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”
ጌታ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ፣ ምድርን ይዳስሳል፤ እርሷም ትቀልጣለች፤ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል።
ነነዌን ግን፣ በሚያጥለቀልቅ ጐርፍ ያጠፋታል፤ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።
“በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤