ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣ የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣ በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤
የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል፤ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።
ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል።
“ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?
እርሱ የድብና የኦሪዮን፣ የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤
ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤ የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ።
ጨለማን ልኮ ምድሪቱን ጽልመት አለበሰ፤ እነርሱም በቃሉ ላይ ማመፅን ተዉ።
ዕውሮችን በማያወቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ። ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ። ይህን አደርጋለሁ፤ አልተዋቸውም።
በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤ አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ ጀንበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤ በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን።
“ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤ ኀይሌንና ታላቅነቴን፣ አሁን አስተምራቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር፣ እንደ ሆነ ያውቃሉ።
“ምድርን የፈጠራት፣ ያበጃትና የመሠረታት እግዚአብሔር፣ ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፣ እርሱ እንዲህ ይላል፤
ተራሮችን የሚሠራ፣ ነፋስን የሚፈጥር፣ ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን፣ ፀሓይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ ምድርንም ደማቅ ብርሃን ሳለ በቀን አጨልማታለሁ።
መኖሪያውን በሰማይ የሚሠራ፣ መሠረቱንም በምድር የሚያደርግ፣ የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣ በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስስ፣ እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።
በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድር ላሉት ብርሃን ወጣላቸው።”
ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣ በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣ እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”