ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እንድትጋዙ አደርጋለሁ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር የሆነ።
እግዚአብሔር እስራኤልን በውሃ ውስጥ እንደሚንቀጠቀጥ ሸንበቆ ያንቀጠቅጠዋል፤ የአሼራን ምስል ዐምድ በመሥራት እግዚአብሔርን ለቍጣ ያነሣሡት ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስራኤልን ይነቅላቸዋል፤ ከወንዙም ማዶ ይበትናቸዋል።
በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን፣ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካን፣ ያኖዋን፣ ቃዴስንና አሦርን፣ ገለዓድንና ገሊላን፣ የንፍታሌምንም ምድር ጭምር ያዘ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰደው።
እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በዚያው ቀጠሉበት፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከሀገሩ ተማርኮ ወደ አሦር ተወሰደ፤ አሁንም በዚያው ይገኛል።
በሆሴዕ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም በምርኮ ወደ አሦር አፈለሳቸው። እነዚህም በአላሔ፣ ጎዛን ውስጥ በአቦር ወንዝ አጠገብ እንዲሁም በማዴ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ብትሰጥ፣ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ አትቃጠልም፤ አንተና ቤተ ሰብህም በሕይወት ትኖራላችሁ።
ተራሮችን የሚሠራ፣ ነፋስን የሚፈጥር፣ ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
ይልቁንም ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን፣ የንጉሣችሁን የሲኩትን ጣዖታት፣ የኮከብ አምላክ የሆነውን የሪፋን አማልክት አንሥታችሁ ተሸከማችሁ።
በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣ በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣ እናንተ የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!
ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናችሁ፤ መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።
ይልቁንም ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን፣ የሞሎክን ድንኳንና የኮከብ አምላክ የሆነውን የሬምፋም ጣዖት አንሥታችሁ ተሸከማችሁ። ስለዚህ ከባቢሎን ማዶ እንድትጋዙ አደርጋለሁ።’