የችግረኞችን ራስ፣ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ ፍትሕንም ከጭቍኖች ይነጥቃሉ፤ አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋራ ይተኛሉ፤ እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።
ይህን በመፈጸምህ ግን፣ የእግዚአብሔር ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፣ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።”
ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ፣ “ዐፅመ ርስቴን አልለቅልህም” ስላለው፣ አክዓብ ተበሳጭቶና ተቈጥቶ ወደ ቤቱ ገባ፤ አኵርፎም በዐልጋው ላይ ተኛ፤ ምግብም መብላት ተወ።
አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤ ሰው ግን ለቍራሽ እንጀራ ሲል በደል ይፈጽማል።
ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!
የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!
እግዚአብሔር፣ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋራ እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
ሕዝቤን በችግር ስታደቅቁት፣ የድኾችንም ፊት በሐዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በውስጥሽ አንዱ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ ሌላውም የልጁን ሚስት ያስነውራል፤ ሌላው ደግሞ የገዛ እኅቱ የሆነችውን የአባቱን ልጅ ይደፍራል።
በአሕዛብ መካከል በሄዱበት ሁሉ ቅዱስ ስሜን አረከሱ፤ ስለ እነርሱ፣ ‘እነዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ናቸው፤ ዳሩ ግን የርሱን ምድር ትተው እንዲሄዱ ተገደዱ’ ተብሏልና።
“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣ የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ አልቀጣቸውም። ወንዶች ከጋለሞቶች ጋራ ይሴስናሉ፤ ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋራ ይሠዋሉና፤ የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!
“ ‘ከምራትህ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከርሷም ጋራ በግብረ ሥጋ አትገናኝ።
“ ‘ከልጆችህ ማንኛውንም ለሞሎክ እንዲሠዋ አሳልፈህ አትስጥ፤ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
“ ‘ከአባትህ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አባትህን ያዋርዳል።
ልጁን ለሞሎክ በመስጠት መቅደሴን አርክሷልና፣ ቅዱሱን ስሜንም አቃልሏልና፣ በዚያ ሰው ላይ ጠላት እሆንበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ።
እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤
እናንተ ድኻውን ትረግጣላችሁ፤ እህል እንዲሰጣችሁም ታስገድዱታላችሁ፤ ስለዚህ በተጠረበ ድንጋይ ቤት ብትሠሩም፣ በውስጡ ግን አትኖሩም፤ ባማሩ የወይን ተክል ቦታዎች ወይን ብትተክሉም፣ የወይን ጠጁን ግን አትጠጡም፤
ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደ ሆነ፣ በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና። ጻድቁን ትጨቍናላችሁ፤ ጕቦም ትቀበላላችሁ፤ በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ።
እናንተ ችግረኞችን የምትረግጡ፣ የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤
ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።
ከሚወድዱት ቤታቸው፣ የሕዝቤን ሴቶች አስወጣችኋቸው፤ ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ።
ሹሞቿ የሚያገሡ አንበሶች፣ ገዦቿ ለነገ የማይሉ፣ የምሽት ተኵላዎች ናቸው።
ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ዘንድ ይሰደባል” ተብሎ እንደ ተጻፈው መሆኑ ነው።
በመካከላችሁ የዝሙት ርኩሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኩሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና።