ከሳውል ጋራ ይጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንንም ባላዩ ጊዜ፣ አፋቸውን ይዘው ቆሙ።
ራእዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርሁ፤ ከእኔ ጋራ የነበሩት ሰዎች አላዩም፤ ነገር ግን ታላቅ ፍርሀት ስለ ወደቀባቸው ሸሽተው ተደበቁ።
በዚያ የነበሩት፣ ድምፁን የሰሙት አያሌ ሰዎች፣ “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ ሌሎች ደግሞ፣ “መልአክ ተናገረው” አሉ።
ከእኔ ጋራ የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የሚናገረኝን የርሱን ድምፅ በትክክል አልሰሙም።