ሰውየውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለማግኘት ዐስቦ በትኵረት ተመለከታቸው።
ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋራ ወደ እርሱ ትኵር ብሎ አየውና፣ “እስኪ ወደ እኛ ተመልከት!” አለው።
ጴጥሮስ ግን፣ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ነገር ግን ያለኝን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ በእግርህ ተመላለስ” አለው፤