ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቍልል ጋራ ተላትሞ መሬት ነካ፤ የፊተኛው ክፍሉም አሸዋው ውስጥ ተቀርቅሮ አልነቃነቅ አለ፤ የኋለኛው ክፍሉም በማዕበሉ ክፉኛ ስለ ተመታ ይሰባበር ጀመር።
ኢዮሣፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ይሁን እንጂ በዔጽዮንጋብር ስለ ተሰበሩ ከቶ ወደዚያ መሄድ አልቻሉም ነበር።
የመሪሳ ሰው የሆነው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር በኢዮሣፍጥ ላይ፣ “ከአካዝያስ ጋራ የስምምነት ውል ስለ አደረግህ፣ እግዚአብሔር ሥራህን ያፈርሰዋል” ሲል ትንቢት ተናገረበት፤ መርከቦቹም ተሰበሩ፤ ለንግዱም ሥራ መሄድ አልቻሉም።
ቀዛፊዎችሽ፣ ወደ ጥልቁ ባሕር ይወስዱሻል፤ የምሥራቁ ነፋስ ግን፣ በባሕሩ መካከል ይሰባብርሻል።
አሁን ግን በጥልቅ ውሃ ውስጥ፣ በባሕር ተንኰታኵተሻል፤ ጭነትሽና ተሳፋሪዎችሽ ሁሉ፣ ከአንቺ ጋራ ሰጥመዋል።
ጀልባዋንም ወደ ላይ ጐትተው ካወጧት በኋላ መርከቧ እንዳትፈራርስ ዙሪያዋን በገመድ ጠምጥመው አሰሯት፤ ስርቲስ ከተባለው አሸዋማ ደለል ጋራ ሄደው እንዳይላተሙ ስለ ፈሩም፣ የመርከቧን ሸራ አውርደው እንዲሁ በዘፈቀደ እንድትነዳ አደረጉ።
መርከበኞቹም ከመርከቡ በስተ ፊት መልሕቅ የሚጥሉ መስለው፣ ትንሿን ጀልባ በማውረድ ከመርከቧ ሊያመልጡ ሞከሩ።
ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ።
ወታደሮቹም ከእስረኞች ማንም ዋኝቶ ለማምለጥ ቢሞክር ለመግደል ተስማሙ።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።