ሁሉም ተበራቱና እንጀራውን ራሳቸው ወስደው በሉ።
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ አይዞህ፣ በርታ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
አሁንም ቢሆን አይዟችሁ፤ መርከቧ እንጂ ከእናንተ አንዲት ነፍስ እንኳ አትጠፋምና።
ስለዚህ፣ እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አይዟችሁ እርሱ እንደ ነገረኝ እንደዚያው እንደሚሆን በእግዚአብሔር አምናለሁና።