Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሐዋርያት ሥራ 26:13

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ሆይ፤ እኩለ ቀን ላይ በመንገድ ሳለሁ፣ ብሩህነቱ ከፀሓይ የሚበልጥ ብርሃን በእኔና በባልንጀሮቼ ዙሪያ ከሰማይ ሲያበራ አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣ በሽማግሌዎቹም ፊት በክብሩ ይነግሣል፤ ጨረቃ ትሸማቀቃለች፤ ፀሓይም ታፍራለች።

እግዚአብሔር የሕዝቡን ስብራት ሲጠግን፣ ያቈሰለውንም ሲፈውስ፣ ጨረቃ እንደ ፀሓይ ታበራለች፤ የፀሓይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት ዕጥፍ ይደምቃል።

በዚያም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሓይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ።

“ስንጓዝም እኩለ ቀን ገደማ ወደ ደማስቆ እንደ ተቃረብሁ፣ ድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ በራ፤

ከእኔ ጋራ የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የሚናገረኝን የርሱን ድምፅ በትክክል አልሰሙም።

“በዚህ መሠረት አንድ ቀን ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ በምጓዝበት ጊዜ፣

ሁላችንም በምድር ላይ ወደቅን፤ እኔም በዕብራይስጥ ቋንቋ፣ ‘ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ? መውጊያውን ብትጋፋ ጕዳቱ በአንተ ይብሳል’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።

ደማስቆ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው፣ ብርሃን ከሰማይ ድንገት በዙሪያው አንጸባረቀበት፤

በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሓይ ነበረ።

የእግዚአብሔር ክብር ብርሃን ስለሚሰጣትና በጉም መብራቷ ስለ ሆነ፣ ከተማዋ ፀሓይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች