ከሳሾቹም ተነሥተው በመቆም ሲናገሩ፣ እኔ ያሰብሁትን ያህል ከባድ ክስ አላቀረቡበትም፤
ጲላጦስም፣ “እናንተ ራሳችሁ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት” አላቸው። አይሁድም፣ “እኛማ በማንም ላይ የሞት ፍርድ ለመፍረድ መብት የለንም” አሉት።
ጳውሎስ ሊናገር ገና አፉን ሲከፍት፣ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፤ “የአይሁድ ሰዎች ሆይ፤ ያቀረባችሁት ጕዳይ ስለ ዐመፅ ወይም ስለ ከባድ ወንጀል ቢሆን ኖሮ ላደምጣችሁ በተገባኝ ነበር፤
ስለዚህ ከሳሾቹ ከእኔ ጋራ ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ ጕዳዩን ሳላጓትት በማግስቱም ችሎት ተቀምጬ ያን ሰው እንዲያቀርቡት አዘዝሁ።
ይልቁን ስለ ገዛ ሃይማኖታቸውና ሞቶ ስለ ነበረው፣ ጳውሎስ ግን ሕያው ነው ስለሚለው ሰው፣ ስለ ኢየሱስ ይከራከሩት ነበር።
ስለዚህ ከባለሥልጣኖቻችሁ መካከል አንዳንዶች ከእኔ ጋራ ይምጡና ሰውየው ጥፋት ካለበት ክሱን በዚያው ያቅርቡ።”