ከሕዝቡ ሁካታ የተነሣ፣ ጳውሎስ ወደ መውጫው ደረጃ ሲደርስ ወታደሮቹ ይሸከሙት ዘንድ ግድ ሆነባቸው።
ጌታ ሆይ፤ ግፍንና ሁከትን በከተማዪቱ ውስጥ አይቼአለሁና፣ ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ።
የለም፤ በልባችሁ ክፋትን ታውጠነጥናላችሁ፤ በእጃችሁም ዐመፅን በምድር ላይ ትጐነጕናላችሁ።
ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለች፤ ከርግማን የተነሣ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ደርቀዋል። ነቢያቱም ጠማማ መንገድ ተከትለዋል፤ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል።
የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፣ ‘እነሆ፤ ፍሬ ለማግኘት ልፈልግባት ሦስት ዓመት ወደዚህች በለስ መጥቼ ምንም አላገኘሁም፤ ስለዚህ ቍረጣት፤ ለምን ዐፈሩን በከንቱ ታሟጥጣለች?’ አለው።
ጳውሎስም የጦር አዛዡን ካስፈቀደ በኋላ፣ በደረጃው ላይ ቆሞ ሕዝቡን በእጁ ጠቀሰ፤ ሁሉም ጸጥ ባሉ ጊዜ፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ አለ፤
ነገር ግን የጦር አዛዡ ሉስዮስ መጥቶ በታላቅ ኀይል ከእጃችን ነጥቆ ወሰደው፤ ከሳሾቹም ወደ አንተ እንዲመጡ አዘዘ።]