ከዚህ በኋላ፣ ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።
ቂሳርያም በደረሰ ጊዜ፣ ወጥቶ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቀረበ፤ ከዚያም ወደ አንጾኪያ ወረደ።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል ዐልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ ወስኖ፣ “እዚያ ከደረስሁ በኋላ ሮምን ደግሞ ማየት አለብኝ” አለ።
ይህን ስንሰማ እኛና በዚያም የሚኖሩት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ለመንነው።
ፊስጦስም ወደ አውራጃው ከገባ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ከቂሳርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
ከእነርሱም ጋራ ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ያህል ከሰነበተ በኋላ፣ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም ፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ።
ፊስጦስም ለአይሁድ በጎ ለመዋል ፈልጎ፣ ጳውሎስን “ስለዚህ ጕዳይ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ በእኔ ፊት ለመፋረድ ፈቃደኛ ነህን?” አለው።