ዳዊትም ስለ እርሱ እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየዋለሁ፤ እርሱ በቀኜ ነውና፣ ከቶ አልታወክም።
በነፍሱ ላይ ከሚፈርዱት ያድነው ዘንድ፣ እርሱ በችግረኛው ቀኝ በኩል ይቆማልና።
ጌታ በቀኝህ ነው፤ በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል።
ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኗልና፤ ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ ከቆመበት አይናወጥም።
እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣ “ከቶ አልናወጥም” አልሁ።
ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።
ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።
ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።
ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዐት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤
እነሆ፤ ሁላችሁም በየፊናችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ጊዜ አሁን ነው። እኔንም ብቻዬን ትተዉኛላችሁ፤ ይሁን እንጂ አባቴ ከእኔ ጋራ ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም በተስፋ ይኖራል።