በጨርቁም ላይ አራት እግር ያላቸው የተለያዩ እንስሳት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና በአየር የሚበርሩ አዕዋፍ ነበሩበት።
ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር።
“ ‘ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ።
የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤
ሰማይም ተከፍቶ አንድ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራት ማእዘን ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድ አየ።
በዚህ ጊዜ፣ “ጴጥሮስ ሆይ፤ ተነሣ፤ እነዚህን ዐርደህ ብላ” የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
አተኵሬም ይህን ነገር ስመለከት አራት እግር ያላቸው እንስሳት፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና በሰማይ የሚበርሩ አዕዋፍ አየሁ።
የዘላለም አምላክን ክብር ምዉት በሆነው ሰው፣ በወፎች፣ በእንስሳትና በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ መስለው ለወጡ።