ዳዊት የአድርአዛር ሹማምት ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው።
ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ አጋዘ።
ካህኑም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው።
ዳዊትም የአድርአዛር ጦር አለቆች ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው።