አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል ቢፈጽም ግን ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።
“ ‘ይሁን እንጂ መንግሥቱን በሙሉ ከእጁ አልወስድበትም፤ ስለ መረጥሁት፣ ትእዛዜንና ሥርዐቴን ስለ ጠበቀው ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እንዲገዛ አድርጌዋለሁ።
“ነገር ግን አንተም ሆንህ ልጆችህ እኔን ከመከተል ወደ ኋላ ብትመለሱ፣ የሰጠኋችሁን ትእዛዞችና ሥርዐቶች ሳትጠብቁ ብትቀሩ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብታመልኳቸው፣
አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንዳራቅሁ ሁሉ፣ ከርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።
ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋኑንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’
እንዲህም አለኝ፤ ‘ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጬዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ።
“እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።
የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አድንሃለሁም’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤ በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።’
እነሆ፤ “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ ከሰማይ ተሰማ።
ነገር ግን ጌታ በሚፈርድብን ጊዜ እንገሠጻለን፤ ይኸውም ከዓለም ጋራ ዐብረን እንዳንኰነን ነው።
“እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፤ ይላል ሁሉን የሚችል ጌታ።”
ስለዚህ ሰው ልጁን እንደሚቀጣ፣ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን እንደሚቀጣህ በልብህ ዕወቅ።
እግዚአብሔር፣ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤” ወይስ ደግሞ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?
ድል የሚነሣ ይህን ሁሉ ይወርሳል፤ እኔም አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።
እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።