Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ሳሙኤል 5:25

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ከገባዖን እስከ ጌዝር ድረስ እያሳደደ መታቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።

ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው።

እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።

እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣ በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።

በዚህ ጊዜ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ፤ ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ ንጉሡንና ሕዝቡን መታቸው።

የዔግሎን ንጉሥ፣ አንድ የጌዝር ንጉሥ፣ አንድ

ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።

ክፊርዓሞናይ፣ ዖፍኒ እንዲሁም ጌባዕ ናቸው፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።

በተራራማው በኤፍሬም አገርም ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች