ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም ነበር። እነዚህ ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
አራተኛው፣ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ ዐምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣
የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ አበኔር በሳኦል ቤት ላይ ኀይሉን ያጠናክር ነበር።
ዐምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።
እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።