ስለዚህም ኢያቡስቴ መልክተኛ ልኮ፣ ሜልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፈልጢኤል ወሰዳት።
በዚህ ጊዜ የሳኦል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር፣ የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፤
ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።
ባሏም እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሏት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “በል ይበቃል! ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው። ስለዚህም ተመለሰ።
የይሳኮር ነገድ መሪ፣ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፤
ሳኦል ግን የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፣ ለጋሊም ተወላጅ ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።