ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።
አንተው ራስህ አስተምረኸኛልና፣ ከድንጋጌህ ዘወር አላልሁም።
መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።
ከአንደበትህ የሚወጣውን ደንብ ሁሉ፣ በከንፈሬ እናገራለሁ።
የእውነትን መንገድ መርጫለሁ፤ ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ።
ወደ ትእዛዞችህ ስመለከት፣ በዚያ ጊዜ አላፍርም።
ትእዛዞችህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው፤ ሰዎች ያለ ምክንያት አሳድደውኛልና ርዳኝ።
ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዐት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤
የማዝዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።
እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ፣ ከሕጉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይቍጠር።
እነዚህን ሕግጋት ብታዳምጥና በጥንቃቄ ብትጠብቃቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ከአንተ ጋራ የገባውን የፍቅር ኪዳኑን ይጠብቃል።
በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ።