ነገር ግን ንጉሡ፣ የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን፤ የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደችለትን ዐምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤
ሳኦልም የኢዮሄልን ልጅ ሪጽፋን በቁባትነት አስቀምጧት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፣ “ለምንድን ነው ከአባቴ ቁባት ጋራ የተኛኸው?” አለው።
እንዲሁም የናሜሲን ልጅ ኢዩን በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ቅባው፤ ደግሞም ነቢይ ሆኖ በእግርህ እንዲተካ የአቤልምሖላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው።
የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፣ የሱዊ፣ ሜልኪሳ ነበሩ፤ ሴቶች ልጆቹም ትልቋ ሜሮብ፣ ትንሿ ሜልኮል ይባሉ ነበር።
ይሁን እንጂ የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤስድሪኤል ተዳረች።