ገባዖናውያንም፣ “ከሳኦልም ሆነ ከቤተ ሰቡ ብር ወይም ወርቅ የመጠየቅ መብት የለንም፤ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፣ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
ላባም፣ “ታዲያ ምን ልስጥህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ምንም አትስጠኝ፤ ነገር ግን የምጠይቅህን አንዲት ነገር ብቻ ብታደርግልኝ ከብቶችህን ማገዴን እቀጥላለሁ፤
“ ‘ነፍስ ያጠፋን፣ በመግደል ወንጀል ተጠያቂ የሆነን ሰው ጉማ አትቀበሉ፤ ፈጽሞ መሞት አለበት።
“ ‘ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ስለ ገባ ስለ ማንኛውም ሰው የደም ዋጋ በመቀበል ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዶ እዚያ እንዲኖር አታድርጉ።