ኢዮአብም አሜሳይን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እንደ ምንድን ነህ?” አለው፤ ከዚያም አሜሳይን የሚስም መስሎ በቀኝ እጁ ጢሙን ያዘው።
እንዲሁም ማንኛውም ሰው ወደ እርሱ ቀርቦ እጅ በሚነሣው ጊዜ፣ አቤሴሎም እጁን ዘርግቶ ይይዘውና ይስመው ነበር።
አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፣ የጽሩያን እኅት፣ የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር።
ንጉሡም፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አኪማአስም፣ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም ባሪያህን ሊልክ ሲል፣ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።
አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ በሁለቱ ሰዎች ላይ አደጋ ጥሎ በሰይፍ ገድሏቸዋልና ስላፈሰሰው ደም እግዚአብሔር ይበቀለዋል። የእስራኤል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔርና የይሁዳ ሰራዊት አዛዥ የዬቴር ልጅ አሜሳይ ሁለቱም ከርሱ የተሻሉና ይበልጥ ትክክለኛ ሰዎች ነበሩ።
አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤ በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።
ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣ በብር ፈሳሽ እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።
ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣ የወዳጅ ማቍሰል ይታመናል።
የናታንያ ልጅ እስማኤልና ዐብረውት የነበሩ ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው፣ የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ የሾመውን የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱት፤ ገደሉትም።
የሚታመን ሰው ከምድር ጠፍቷል፤ አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፤ ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።
እስራኤላውያን እንደ ገና ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ግራኙን ናዖድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ናዖድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።