Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ሳሙኤል 19:35

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፤ ታዲያ ደግና ክፉውን መለየት እችላለሁ? ከእንግዲህ አገልጋይህ የሚበላውንና የሚጠጣውን ጣዕሙን መለየት ይችላል? የሚዘፍኑትን የወንዶችና የሴቶችን ድምፅ አሁንም መስማት እችላለሁ? ታዲያ አገልጋይህ ለንጉሥ ጌታዬ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡም፣ “ልጄ ሆይ፣ ሁላችንም መሄድ የለብንም፤ ሸክም እንሆንብሃለን” ሲል መለሰለት። አቤሴሎም አጥብቆ ቢለምነውም ንጉሡ መሄድ አልፈለገም፤ ነገር ግን መርቆ አሰናበተው።

ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለው፤ “ዐብረኸኝ ብትሄድ ሸክም ትሆንብኛለህ፤

አገልጋይህ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከንጉሡ ጋራ ጥቂት መንገድ ይሄዳል፤ ነገር ግን ንጉሡ በዚህ ሁኔታ ወሮታ የሚመልስልኝ ለምንድን ነው?

ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።

ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።

ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?

ክፋት በአንደበቴ አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?

የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን።

ማንኛውም ቤተ ሰብ ለአንድ ሙሉ ጠቦት ቍጥሩ አነስተኛ ከሆነ፣ በጎረቤት ያሉትን ሰዎች ቍጥር እስከ ቅርብ ከሆነው ጋራ መካፈል ይኖርበታል፤ እያንዳንዱ ሰው በሚበላው መጠንም ምን ያህል ጠቦት እንደሚያስፈልግ መወሰን ይኖርባችኋል።

የፈርዖንም ልጅ፣ “መልካም፣ ሂጂ” አለቻት። ልጅቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ይዛ መጣች።

ለራሴም ብርንና ወርቅን፣ የነገሥታትና የአውራጃዎችን ሀብት አካበትሁ፤ ወንድና ሴት አዝማሪዎች፣ የሰው መደሰቻ የሆኑ ቅምጦች ነበሩኝ።

ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።

ጌታ መልካም መሆኑን ቀምሳችኋልና።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች