ንጉሡም እጅግ ዐዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” ይል ነበር።
እስማኤል ልጁ ስለ ሆነ ነገሩ አብርሃምን እጅግ አስጨነቀው።
የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ።
ለኢዮአብ፣ “ንጉሡ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አቤሴሎም እያለቀሰ እያዘነ ነው” ተብሎ ተነገረው።
ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” እያለ ጮኸ።
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።
አሁን ግን አቤቱ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ አለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስሰኝ።”
የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤ ለወለደችውም ምሬት ይሆንባታል።
ለወገኖቼ ስል ስለ ወንድሞቼ እኔ ራሴ የተረገምሁና ከክርስቶስም ተለይቼ የተጣልሁ እንድሆን እንኳ እወድድ ነበር፤
ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም።