ንጉሡም፣ “ዕልፍ በልና ቁም” አለው፤ ስለዚህ ዕልፍ ብሎ ቆመ።
ንጉሡም፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አኪማአስም፣ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም ባሪያህን ሊልክ ሲል፣ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።
ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ እግዚአብሔር ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው።