ኩሲ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፣ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ እርሱ ያለውን እናድርግ? ካልሆነም እስኪ የአንተን ሐሳብ ንገረን” አለው።
አቤሴሎም ግን፣ “እስኪ ደግሞ አርካዊውን ኩሲን ጥሩትና የሚለውን እንስማ” አለ።
ኩሲም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “አኪጦፌል የሰጠው ምክር በዚህ ጊዜ የሚያዋጣ አይደለም፤