አኪጦፌልም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰው መርጬ፣ በዛሬዪቱ ሌሊት ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤
በዚያም ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ምክር ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ይቈጠር ነበር፤ ዳዊትም ሆነ አቤሴሎም የአኪጦፌልን ምክር የሚቀበሉት በዚህ ሁኔታ ነበር።
በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜም አደጋ እጥልበታለሁ፤ ሽብር እለቅበታለሁ፤ ከዚያም ዐብሮት ያለው ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻ እመታዋለሁ፣
በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።
እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤ ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው።
ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ በዐይናቸው አይዞርም።