እኔ አገልጋይህ በሶርያ ምድር በጌሹር ሳለሁ ‘እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም የመለሰኝ እንደ ሆነ፣ በኬብሮን ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስያለሁ።”
ከዚያም ኢዮአብ ወደ ጌሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አመጣው።
አቤሴሎምም፣ ኢዮአብን፣ “ከጌሹር ለምን መጣሁ? ‘ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና’ ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን፤ የንጉሡን ዐይን ማየት እፈልጋለሁ፤ ምንም ዐይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው።
ንጉሡም፣ “በሰላም ሂድ” አለው፤ ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ኬብሮን ሄደ።
ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ፣ ሦስተኛው፣ ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣
እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተ ስእለት አለብኝ፤ የማቀርብልህም የምስጋና መሥዋዕት ነው፤
ለአምላክ ስእለትን በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፤ በሞኞች ደስ አይለውምና፤ ስእለትህን ፈጽም።
እናንተ፣ “ከሞት ጋራ ቃል ኪዳን ገብተናል፤ ከሲኦልም ጋራ ስምምነት አድርገናል፤ ውሸትን መጠጊያችን፣ ሐሰትን መደበቂያችን አድርገናል፤ ታላቅ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ ሊነካን አይችልም” በማለት ታብያችኋል።
‘ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተት ፈጸማችሁ።
እግዚአብሔርን ማምለክ የማያስፈልግ መስሎ ከታያችሁ ግን፣ የቀድሞ አባቶቻችሁ ከወንዙ ማዶ ካመለኳቸው አማልክት ወይም በምድራቸው የምትኖሩባቸው አሞራውያን ከሚያመልኳቸው አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።”
ሳሙኤል ግን፣ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፣ ‘ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል።