ከዚያም ኢዮአብ ወደ አቤሴሎም ቤት ሄደ፣ “አገልጋዮችህ ለምንድን ነው ዕርሻዬን ያቃጠሉት?” ብሎ ጠየቀው።
ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ የኢዮአብ ዕርሻ የሚገኘው ከእኔ ዕርሻ አጠገብ ነው፤ በዕርሻው ላይ የገብስ አዝመራ አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው የኢዮአብን ዕርሻ በእሳት አቃጠሉት።
አቤሴሎምም፣ ኢዮአብን፣ “ከጌሹር ለምን መጣሁ? ‘ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና’ ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን፤ የንጉሡን ዐይን ማየት እፈልጋለሁ፤ ምንም ዐይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው።