Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ሳሙኤል 14:11

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሷም፣ “ደም ተበቃዮቹ ልጄን በማጥፋት የባሰ ጕዳት እንዳያደርሱ፣ ንጉሡ አምላኩን እግዚአብሔርን ይለምን” አለች። ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ከልጅሽ ራስ ላይ አንዲት ጠጕር እንኳ አትነካም” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራም ግን ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ልዑል አምላክ እጆቼን አንሥቻለሁ፤

ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎች ሚስቶች በላያቸው ላይ ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋራ ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።”

ንጉሡም፣ “ማንም ሰው አንዳች ነገር ቢናገርሽ እኔ ዘንድ አምጪው፤ ዳግም አያስቸግርሽም” ሲል መለሰላት።

ከዚያም ሴቲቱ፣ “እኔ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ” አለችው። እርሱም፣ “ዕሺ ተናገሪ” አላት።

ንጉሡም ኢዮአብን፣ “መልካም ነው፤ ፈቅጃለሁ፤ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው።

ሰሎሞንም፣ “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ጥፋት ከተገኘበት ግን ይሞታል” ሲል መለሰ።

በእውነት፣ በቅንነትና በጽድቅ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለህ ብትምል፣ አሕዛብ በርሱ ይባረካሉ፤ በርሱም ይከበራሉ።”

ደም መላሹም ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው፤ ባገኘውም ጊዜ ይግደለው።

ወይም ደግሞ በጥላቻ ተነሣሥቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት፣ ያ ሰው በሞት ይቀጣል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም መላሹም ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይግደለው።

ደም ተበቃዩም ከከተማው ውጭ ካገኘው፣ ተከሳሹን ሊገድለው ይችላል፤ በነፍሰ ገዳይነትም አይጠየቅም።

የራስ ጠጕራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው።

ስለዚህ፣ ለደኅንነታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጕር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።”

ሕዝቡ ግን ሳኦልን፣ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? አይደረግም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።

ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፣ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል እግዚአብሔር ለዘላለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በእግዚአብሔር ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።

ሳኦልም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ቅጣት አያገኝሽም” ሲል በእግዚአብሔር ስም ማለላት።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች