አምኖን እኅቱን ትዕማርን ከማፍቀሩ የተነሣ እስኪታመም ድረስ ተጨነቀ፤ ድንግል ስለ ሆነች እርሷን ማግኘት የማይቻል ሆኖ አግኝቶታልና።
የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቈንጆ እኅት ነበረችው፤ እርሷንም የዳዊት ልጅ አምኖን ወደዳት።
አምኖን ኢዮናዳብ የተባለ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ነው። ኢዮናዳብ እጅግ ተንኰለኛ ሰው ነበር።
ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ፣ “ዐፅመ ርስቴን አልለቅልህም” ስላለው፣ አክዓብ ተበሳጭቶና ተቈጥቶ ወደ ቤቱ ገባ፤ አኵርፎም በዐልጋው ላይ ተኛ፤ ምግብም መብላት ተወ።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እማጠናችኋለሁ፤ ውዴን ካገኛችሁት፣ ምን ትሉት መሰላችሁ? በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ወደ ድነት ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም። ዓለማዊ ሐዘን ግን ለሞት ያበቃል።