ሴቲቱ ፀነሰች፤ ለዳዊትም፣ “አርግዣለሁ” ብላ ላከችበት።
ስለዚህም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ስደደው” ሲል ላከበት፤ ኢዮአብም ወደ ዳዊት ላከው።
ቅናት የባልን ቍጣ ይቀሰቅሳልና፤ በሚበቀልበትም ጊዜ ምሕረት አያደርግም።
“ ‘አንድ ሰው ከባልንጀራው ሚስት ጋራ ቢያመነዝር፣ አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ይገደሉ።
አንድ ሰው፣ ከሌላ ሰው ሚስት ጋራ ተኝቶ ቢገኝ፣ ዐብሯት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ፤ ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለብህ።