ከዚያም ባለፍላጻዎቹ ከግንቡ ላይ ሆነው በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ስለ ለቀቁ፣ ከንጉሡ አገልጋዮች ጥቂቶቹን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ።”
መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ ዐየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳድደን መለስናቸው።
ዳዊትም፣ መልእክተኛውን፣ “እንግዲህ እንዲህ ብለህ ይህን ለኢዮአብ ንገረው፤ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ትበላለችና በዚህ አትዘን፤ በከተማዪቱ ላይ ጦርህን አጠንክር’ ” አለው።
“እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”
ዳዊትም ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፣ “ወደ ሳኦል ሰፈር ዐብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፣ “እኔ ዐብሬህ እወርዳለሁ” አለ።