ዳዊት ይህን ሲሰማ፣ ኢዮአብን ከመላው ተዋጊ ሰራዊት ጋራ ላከው።
አሞናውያን፣ ዳዊት እንደ ጠላቸው ባወቁ ጊዜ፣ ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺሕ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥ ከአንድ ሺሕ ሰዎቹ ጋራ ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰዎች ቀጠሩ።
አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የሱባና የረአብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ።