የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ግንባር አሰለፋቸው።
ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።
ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፣ በእስራኤል ጀግንነታቸው ከታወቀው ጥቂቶቹን መርጦ በሶርያውያን ግንባር አሰለፋቸው።
ዳዊትም ሰራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጋታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሰራዊቱ፣ “እኔ ራሴም ዐብሬአችሁ በርግጥ እወጣለሁ” አላቸው።
የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ እርሱም ዝናን ያተረፈ ሰው ነበረ።
የጽሩያ ልጅ አቢሳ በጨው ሸለቆ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ኤዶማውያን ገደለ።
ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።