“ኀያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት ወደቁ! ዮናታን በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል።
“እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል፤ ኀያላኑ እንዴት እንደዚህ ይውደቁ!
“እናንተ የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፣ ልብሶቻችሁንም በወርቀ ዘቦ ላስጌጠላችሁ፣ ለሳኦል አልቅሱለት።
“ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ከንቱ ይሁኑ!”
አክሊላችን ከራሳችን ላይ ወድቋል፤ ወዮልን፤ ኀጢአት ሠርተናልና!
የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ የንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብቶች አደረጉ።