አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች። እርሷም የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።
ተደፍቼም ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ ለጌታዬ ወንድም የልጅ ልጅ የሆነችውን ቈንጆ፣ ለጌታዬ ልጅ እንዳገኝለት በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬ የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።
ሆኖም የዖምሪ ተከታዮች ከጎናት ልጅ ከታምኒ ተከታዮች ይልቅ በረቱ፤ ስለዚህ ታምኒ ሞተ፤ ዖምሪም ነገሠ።
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት፣ ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ፤ ከዚህም ውስጥ ስድስቱን ዓመት የገዛው በቴርሳ ሆኖ ነው።
የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ፣ ንጉሣውያን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች።
አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች፤ እርሷም የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።