ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው፤ ልብናም በዚሁ ጊዜ ዐምፆ ነበር።
በሰይፍ ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ። አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ ወዲያ ትጥላለህ።”
የጦር አዛዡም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ትቶ መሄዱን ሲሰማ ተመለሰ፤ ንጉሡም ልብናን ሲወጋ አገኘው።
በይሆራም ዘመነ መንግሥት፣ ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐምፆ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።
በኢዮራም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?
ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው፤ ልብናም በዚሁ ጊዜ ዐመፀ። ይሆራም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ትቶ ነበርና።
ኤዶማውያን እንደ ገና መጥተው በይሁዳ ላይ አደጋ በመጣል ምርኮኞችን ወስደው ነበርና።
ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፣ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
እንደዚሁም ለነፍሰ ገዳይ የመማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነመሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤