የእግዚአብሔርም ሰው፣ “በየት በኩል ነው የወደቀው?” ሲል ጠየቀ። ቦታውን ባሳየውም ጊዜ ኤልሳዕ ዕንጨት ቈርጦ ወደ ውሃው ውስጥ በመጣል መጥረቢያውን እንዲንሳፈፍ አደረገው።
ከዚያም ወደ ውሃው ምንጭ ሄዶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’ አለ።”
ኤልሳዕም፣ “እስኪ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም።
ከእነርሱም አንዱ ዛፍ እየቈረጠ ሳለ፣ መጥረቢያው በርሮ ከውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፣ “ወየው ጌታዬ፤ የተውሶ መጥረቢያ እኮ ነው!” ብሎ ጮኸ።
ከዚያም፣ “በል አውጣና ውሰደው” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘርግቶ ወሰደው።
ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔር አንዲት ዛፍ አሳየው፤ ዕንጨቷንም ወደ ውሃው ጣላት፤ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ። በዚያም እግዚአብሔር ሕግና ሥርዐት አበጀላቸው፤ በዚያም ስፍራ ፈተናቸው።