ኤልሳዕ ከሽማግሌዎቹ ጋራ በመነጋገር ላይ ሳለም፣ መልእክተኛው ወደ እርሱ ወረደ። ንጉሡም ደርሶ፣ “ይህ ጥፋት የመጣው ከእግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ እኔ ከእግዚአብሔር ምን እጠብቃለሁ?” አለ።
ቃየንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ቅጣቴ ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው።
የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ወዮ! እግዚአብሔር እኛን ሦስት ነገሥታት የጠራን ለሞዓብ አሳልፎ ሊሰጠን ነውን?” አለ።
ኤልሳዕም፣ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በነገው ዕለት በዚሁ ሰዓት፣ በሰማርያ በር አንድ መስፈሪያ ማለፊያ ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ይሸጣል’ ” አለ።
እስኪ፣ እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ንካበት፤ በርግጥ ፊት ለፊት ይረግምሃል።”
እንዲህም አለ፤ “ዕራቍቴን ከእናቴ ማሕፀን ወጣሁ፤ ዕራቍቴንም እሄዳለሁ። እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።”
በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣ እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው?
እስኪ እጅህን ዘርግተህ ዐጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፤ በርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል።”
ሚስቱም፣ “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን? ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” አለችው።
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ አይዞህ፣ በርታ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።
ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።
ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ ተስፋዬ ከርሱ ዘንድ ነውና።
ሰው በራሱ ቂልነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል።
በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።
ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፤ በርሱ እታመናለሁ።
ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።
እግርሽ እስኪነቃ አትሩጪ፤ ጕረሮሽም በውሃ ጥም እስኪደርቅ አትቅበዝበዢ። አንቺ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤ ባዕዳን አማልክትን ወድጃለሁ፤ እነርሱን እከተላለሁ’ አልሽ።
ጌታ ካላዘዘ በቀር፣ ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው?
ታዲያ ሕያው ሰው በኀጢአቱ ሲቀጣ፣ ስለ ምን ያጕረመርማል?
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘እንዲህ ትላላችሁ፤ “በደላችንና ኀጢአታችን ከብዶናል፤ ከዚህም የተነሣ ልንጠፋ ነው፤ ታዲያ እንዴት መኖር እንችላለን?” ’
የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና፤ ስለ መጨረሻውም ይናገራል፤ እርሱም አይዋሽም፤ የሚዘገይ ቢመስልም ጠብቀው፤ በርግጥ ይመጣል፤ ከቶም አይዘገይም።
ደቀ መዛሙርቱ ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ እንደሚገባቸው ለማሳየት ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤
ይህንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ የርሱን ዕቅድ አንስተውምና።
ደግሞም ከልክ በላይ ዐዝኖ ተስፋ እንዳይቈርጥ፣ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል።
ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ሸለፈታሞች መጥተው መሣለቂያ እንዳያደርጉኝ፣ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፣ ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።